ኦሪት ዘጸአት 36:1-35
Ethiopian Amharic Bible (AMH)
1ለመቅደስም ማገልገያ ሥራ ሁሉ ያደርጉ ዘንድ እንዲያውቁ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን የሰጣቸው ባስልኤልና ኤልያብ በልባቸው ጥበበኞችም ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ነገር ሁሉ አደረጉ።
2ሙሴም ባስልኤልንና ኤልያብን፥ እግዚአብሔርም በልቡ ጥበብን ያደረገለትን በልብ ጥበበኛ ሰው ሁሉ፥ ሥራውንም ለመሥራት ይቀርብ ዘንድ ልቡ ያስነሣውን ሁሉ ጠራቸው።
3እነርሱም የእስራኤል ልጆች ለመቅደስ ማገልገያ ሥራ ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ይሠሩ ዘንድ ከሙሴ ተቀበሉ። እነዚያም እንደ ፈቃዳቸው ማለዳ ማለዳ ስጦታውን ገና ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።
4የመቅደሱንም ሥራ የሚሠሩ ጠቢባን ሁሉ የሚያደርጉትን ሥራ ትተው መጡ፥
5እነርሱም ሙሴን። እግዚአብሔር ለማገልገያ ሥራ ይደረግ ዘንድ ላዘዘው ከሚበቃ ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ሕዝቡ አመጡ ብለው ተናገሩት።
7ያመጡትም ነገር ሥራን ሁሉ ለመፈጸም በቅቶ ገና ይተርፍ ስለ ነበረ ሙሴ አዘዘና። ወንድ ወይም ሴት ለመቅደስ ስጦታ ከዚህ የበለጠ የሚያመጣ አይኑር ብሎ በሰፈሩ ውስጥ አሳወጀ። ሕዝቡም እንዳያመጡ ተከለከሉ። ፕ
8በእነርሱም ዘንድ ያሉት ሥራ ሲሠሩ የነበሩት በልባቸው ጥበበኞች ሁሉ ማደሪያውን ከአሥር መጋረጆች ሠሩ፤ እነርሱንም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊም ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ሠሩ፤ በእነርሱም ላይ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤልን አደረጉባቸው።
9የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመት ሀያ ስምንት ክንድ፥ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ፤ የመጋረጆቹ ሁሉ ልክ ትክክል ነበረ።
10አምስቱንም መጋረጆች እርስ በርሳቸው አጋጠሙ፤ አምስቱንም መጋረጆች እንዲሁ እርስ በርሳቸው አጋጠሙ።
11ከሚጋጠሙትም መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አደረጉ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አደረጉ።
12አምሳ ቀለበቶችንችን በአንድ መጋረጃ አደረጉ፤ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አደረጉ፤ ቀለበቶቹ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት የሚተያዩ ነበሩ።
13አምሳም የወርቅ መያዣዎች ሠሩ፤ መጋረጆችንም እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጠሙአቸው፤ አንድ ማደሪያም ሆነ።
14ከማደሪያውም በላይ ለድንኳን የሚሆኑ መጋረጆችን ከፍየል ጠጕር አደረጉ፤ አሥራ አንድ መጋረጆች አደረጉ።
15እያንዳንዱም መጋረጃ ርዝመቱ ሠላሳ ክንድ፥ እያንዳንዱም መጋረጃ ወርዱ አራት ክንድ ነበረ፤ የአሥራ አንዱም መጋረጆች መጠናቸው ትክክል ነበረ።
16አምስቱንም መጋረጆች እርስ በርሳቸው አንድ አድርገው፥ ስድስቱንም መጋረጆች አንድ አድርገው አጋጠሙአቸው።
17ከተጋጠሙትም መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አደረጉ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አደረጉ።
19ለማደሪያውም ከግራር እንጨት የሚቆሙትን ሳንቆች አደረጉ።
20የሳንቃው ሁሉ ርዝመቱ አሥር ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ።
21ለእያንዳንዱም ሳንቃ አንዱን በአንዱ ላይ የሚያያይዙ ሁለት ማጋጠሚያዎች ነበሩ፤ ለማደሪያው ሳንቆች ሁሉ እንዲሁ አደረጉ።
22ለማደሪያውም በደቡብ ወገን ሀያ ሳንቆችን አደረጉ፤
23ከሀያውም ሳንቆች በታች አርባ የብር እግሮች አደረጉ፤ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ለሁለቱ ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ነበሩ።
24ለማደሪያው ለሁለተኛው ወገን በሰሜን በኩል ሀያ ሳንቆች አደረጉ፤
25ለእነርሱም አርባ የብር እግሮች፥ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግሮች አደረጉ።
26ለማደሪያውም በምዕራቡ ወገበስተ ኋላ ስድስት ሳንቆች አደረጉ።
27ለማደሪያውም ለሁለቱ ማዕዘን በስተ ኋላ ሁለት ሳንቆች አደረጉ።
28ከታችም እስከ ላይ እስከ አንደኛው ቀለበት ድረስ አንድ ሳንቃ ድርብ ነበረ፤ ለሁለቱም ማዕዘን እንዲሁ ሁለት ነበሩ።
29ስምንት ሳንቆችና አሥራ ስድስቱ የብር እግሮቻቸው፥ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት ሁለት እግሮች ነበሩ።
30ከግራርም እንጨት በማደሪያው በአንደኛው ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎች፥
31በማደሪያውም በሁለተኛው ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎች፥ ከማደሪያውም በስተ ኋላ በምዕራቡ ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎች አደረጉ።
32መካከለኛውንም መወርወሪያ በሳንቆቹ መካከል ከዳር እስከ ዳር አሳለፉ።
33ሳንቆቹንም በወርቅ ለበጡአቸው፤ ቀለበቶቻቸውንም የመወርወሪያ ቤት እንዲሆኑላቸው ከወርቅ አደረጉ፤ መወርወሪያዎቹንም በወርቅ ለበጡአቸው።
34መጋረጃውንም ከሰማያዊና ከሐምራዊ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ አደረጉ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤልን በእርሱ ላይ አደረጉ።
35ከግራርም እንጨት አራት ምሰሶች አደረጉለት፥ በወርቅም ለበጡአቸው፤ ኩላቦቻቸው የወርቅ ነበሩ፤ ለእነርሱም አራት የብር እግሮች አደረጉ።
36ለድንኳኑም ደጃፍ ከሰማያዊና ከሐምራዊ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ በጥልፍ አሠራር የተሠራ መጋረጃ አደረጉ፤
37አምስቱንም ምሰሶች፥ ኩላቦቻቸውንም አደረጉ፤ ጕልላቶቻቸውንና ዘንጎቻቸውንም በወርቅ ለበጡአቸው፤ አምስቱም እግሮቻቸው የናስ ነበሩ።