መጽሐፈ ዕዝራ። 2:1-66
Ethiopian Amharic Bible (AMH)
1የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
2ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዕላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጉዋይ፥ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ።
3የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ የፋሮስ ልጆች፥ ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት።
4የሰፋጥያስ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት።
5የኤራ ልጆች፥ ሰባት መቶ ሰባ አምስት።
6ከኢያሱና ከኢዮአብ ልጆች የሆኑ የፈሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አሥራ ሁለት።
7የኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።
8የዛቱዕ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት።
9የዘካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ።
10የባኒ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት።
11የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ሦስት።
12የዓዝጋድ ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ ሀያ ሁለት።
13የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት።
14የበጉዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ አምሳ ስድስት።
15የዓዲን ልጆች፥ አራት መቶ አምሳ አራት።
16ከሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት።
17የቤሳይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ ሦስት።
18የዮራ ልጆች፥ መቶ አሥራ ሁለት።
19የሐሱም ልጆች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት።
21የነጦፋ ሰዎች፥ አምሳ ስድስት።
22የዓናቶት ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት።
23የዓዝሞት ልጆች፥ አርባ ሁለት።
24የቂርያትይዓሪምና የከፊራ የብኤሮትም ልጆች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት።
25የራማና የጌባ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ።
26የማክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት።
27የቤቴልና የጋይ ሰዎች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት።
28የናባው ልጆች፥ አምሳ ሁለት።
29የመጌብስ ልጆች፥ መቶ አምሳ ስድስት።
30የሁለተኛውም ኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።
31የካሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ።
32የሎድና የሐዲድ የኦኖም ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አምስት።
33የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት።
34የሴናዓ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሳ።
35ካህናቱ፤ ከኢያሱ ወገን የዮዳኤ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት።
36የኢሜር ልጆች፥ ሺህ አምሳ ሁለት።
37የፋስኮር ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት።
38የካሪም ልጆች፥ ሺህ አሥራ ሰባት።
39ሌዋውያኑ፤ ከሆዳይዋ ወገን የኢያሱና የቀድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት።
40መዘምራኑ፤ የአሳፍ ልጆች፥ መቶ ሀያ ስምንት።
41የበረኞች ልጆች፤ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ።
42ናታኒም፤ የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥
43የጠብዖት ልጆች፥ የኬራስ ልጆች፥ የሲዓ ልጆች፤
44የፋዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥
45የአጋባ ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የአጋብ ልጆች፥ የሰምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥
46የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ የራያ ልጆች፥
47የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥
48የጋሴም ልጆች፥ የዖዛ ልጆች፥ የፋሴሐ ልጆች፥
49የቤሳይ ልጆች፥ የአስና ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥ የንፉሰሲም ልጆች፥
50የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቁፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥
51የበስሎት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥
52የሐርሳ ልጆች፥ የበርቆስ ልጆች፥
53የሲሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች።
54የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች፤ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥
55የየዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥
56የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈክራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች።
57እነዚህ ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።
58ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ነበሩ፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፤
59የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት ነበሩ።
60ከካህናቱም ልጆች፤ የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች።
61እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አልተገኘም፥ ከክህነትም ተከለከሉ።
62ሐቴርሰታም። በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ድረስ ከቅዱሰ ቅዱሳን አትበሉም አላቸው።
64ፈረሶቻቸውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት በቅሎቻቸውም ሁለት መቶ አርባ አምስት፥
65ግመሎቻቸውም አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ።
66በኢየሩሳሌምም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአባቶች ቤቶች አለቆች አያሌዎች ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው ይሠራ ዘንድ በፈቃዳቸው ሰጡ።
67ስድሳ አንድ ሺህም የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህም ምናን ብር፥ አንድ መቶም የካህናት ልብስ እንደ ችሎታቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ።
68ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ ከሕዝቡም አያሌዎች፥ መዘምራኑና በረኞቹም፥ ናታኒምም በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።