መጽሐፈ ኢዮብ። 35:1-14
Ethiopian Amharic Bible (AMH)
1ኤሊሁም ደግሞ መለሰ እንዲህም አለ።
2ይህ ጽድቅ እንደ ሆነ ታስባለህን? ወይስ። በእግዚአብሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ ትላለህን?
3አንተ። ምን ጥቅም አለህ? ኃጢአት ሠርቼ ከማገኘው ይልቅ ኃጢአት ባልሠራ ኖሮ ምን እጠቀማለሁ? ብለህ ጠይቀሃልና።
4እኔ ለአንተና ከአንተ ጋር ላሉ ለባልንጀሮችህ እመልሳለሁ።
5ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ እይ፤ ከአንተም ከፍ ከፍ ያሉትን ደመናት ተመልከት።
6ኃጢአት ብትሠራ ምን ትጐዳዋለህ? መተላለፍህስ ቢበዛ ምን ታደርገዋለህ?
7ጻድቅስ ብትሆን ምን ትሰጠዋለህ? ወይስ ከእጅህ ምንን ይቀበላል?
8እንደ አንተ ያለውን ሰው ክፋትህ ይጐዳዋል፤ ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል።
9ከግፍ ብዛት የተነሣ ሰዎች ይጮኻሉ፤ ከኃያላንም ክንድ የተነሣ ለእርዳታ ይጠራሉ።
11በዚያ ስለ ክፉ ሰዎች ትዕቢት ይጮኻሉ፥ እርሱ ግን አይመልስላቸውም።
12በእውነት እግዚአብሔር ከንቱ ነገርን አይሰማም፥ ሁሉን የሚችል አምላክም አይመለከተውም፤
13ይልቁንም። አላየውም፤ ነገሩ በእርሱ ፊት ነው፥ እኔም አጠብቀዋለሁ ስትል።
14አሁን ግን በቍጣው አልጐበኘምና። በኃጢአት እጅግ አያስብም ትላለህ።
15ስለዚህ ኢዮብ አፉን በከንቱ ይከፍታል፥ ያለ እውቀትም ቃሉን ያበዛል።