መጽሐፈ ነህምያ። 10:1-23
Ethiopian Amharic Bible (AMH)
1ያተሙትም እነዚህ ናቸው፤ የሐካልያ ልጅ ሐቴርሰታ ነህምያ፥
2ሴዴቅያስ፥ ሠራያ፥
3ዓዛርያስ፥ ኤርምያስ፥ ፋስኮር፥ አማርያ፥ መልክያ፥
5ሐጡስ፥ ሰበንያ፥ መሉክ፥ ካሪም፥
6ሜሪሞት፥ አብድዩ፥ ዳንኤል፥ ጌንቶን፥ ባሮክ፥
8ሜሱላም፥ አብያ፥ ሚያሚን፥ መዓዝያ፥ ቤልጋል፥ ሸማያ፤ እነዚህ ካህናት ነበሩ።
9ሌዋውያኑም፤ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ ከኤንሐዳድ ልጆች ቢንዊ፥ ቀድምኤል፤
10ወንድሞቻቸውም ሰባንያ፥ ሆዲያ፥ ቆሊጣስ፥
11ፌልያ፥ ሐናን፥ ሚካ፥ ረአብ፥ ሐሸብያ፥
13የሕዝቡ አለቆች፤ ፋሮስ፥ ፈሐት ሞዓብ፥
14ኤላም፥ ዛቱዕ፥ ባኒ፥ ቡኒ፥ ዓዝጋድ፥ ቤባይ፥
16ዓዙር፥ ሆዲያ፥ ሐሱም፥ ቤሳይ፥
19ሐናን፥ ዓናያ፥ ሆሴዕ፥ ሐናንያ፥ አሱብ፥
22የቀሩትም ሕዝብ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በረኞቹም፥ መዘምራንም፥ ናታኒምም፥ ከምድርም አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ሕግ ራሳቸውን የለዩ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸውም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉትም ሁሉ ወደ ወንድሞቻቸው ወደ ታላላቆቻቸው ተጠጉ፤
23በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የጌታችንንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ፍርዱንም ሥርዓቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ እርግማንና መሐላውን አደረጉ።
24ሴቶች ልጆቻችንንም ለምድር አሕዛብ አንሰጥም፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለልጆቻችን አንወስድም፤
25የምድርን አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ፥ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ የሰባተኛውንም ዓመት ፍሬና ዕዳን ማስከፈል እንተዋለን ብለው ማሉ።
27እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቍርባን ዕጣ ተጣጣልን፤
28በየዓመቱም የመሬታችንን በኵራት የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ሁሉ በኵራት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥
29በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
30የእህላችንንም በኵራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቍርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን።
31ሌዋውያኑም አሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፤ ሌዋውያኑም የአሥራቱን አሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።
32የእስራኤል ልጆችና የሌዊ ልጆችም የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም የማንሣት ቍርባንን የመቅደሱ ዕቃዎችና የሚያገለግሉት ካህናት በረኞቹና መዘምራኑ ወዳሉባቸው ጓዳዎች ያግቡት፤ እንዲሁም የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም።