መጽሐፈ ነህምያ። 12:1-44

Ethiopian Amharic Bible (AMH)

1ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር የወጡት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤

2ሠራያ፥ ኤርምያስ፥ ዕዝራ፥ አማርያ፥

3መሉክ፥ ሐጡስ፥ ሴኬንያ፥ ሬሁም፥ ሜሪሞት፥

5አዶ፥ ጌንቶን፥ አብያ፥ ሚያሚን

6መዓድያ፥ ቢልጋ፥ ሸማያ፥ ዮያሪብ፥ ዮዳኤ፥

7ሰሉ፥ ዓሞቅ፥ ኬልቅያስ፥ ዮዳኤ፤ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ።

8ሌዋውያኑም፤ ኢያሱ፥ ቢንዊ፥ ቀድምኤል፥ ሰራብያ፥ ይሁዳ፥ ከወንድሞቹም ጋር በመዘምራን ላይ የነበረ መታንያ።

9ወንድሞቻቸውም በቅቡቅያና ዑኒ በየሰሞናቸው በአንጻራቸው ነበሩ።

10ኢያሱም ዮአቂምን ወለደ፥ ዮአቂምም ኤልያሴብን ወለደ፥ ኤልያሴብም ዮአዳን ወለደ፥

11ዮአዳም ዮናታንን ወለደ፥ ዮናታንም ያዱአን ወለደ።

12በዮአቂምም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች እነዚህ ካህናቱ ነበሩ፤ ከሠራያ ምራያ፥

13ከኤርምያስ ሐናንያ፥ ከዕዝራ ሜሱላም፥

14ከአማርያ ይሆሐናን፥ ከመሉኪ ዮናታን፥

15ከሰበንያ ዮሴፍ፥ ከካሪም ዓድና፥ ከመራዮት ሔልቃይ፥

16ከአዶ ዘካርያስ፥ ከጌንቶን ሜሱላም፥

17ከአብያ ዚክሪ፥ ከሚያሚን ሞዓድያ፥

18ፈልጣይ፥ ከቢልጋ ሳሙስ፥ ከሸማያ ዮናታን፥

19ከዮያሪብ መትናይ፥ ከዮዳኤ ኦዚ፥

20ከሳላይ ቃላይ፥ ከዓሞቅ ዔቤር፥

21ከኬልቅያስ ሐሸብያ፥ ከዮዳኤ ናትናኤል።

22ከሌዋውያኑም በኤልያሴብና በዮአዳ፥ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ተጻፉ፤ ካህናቱም በፋርሳዊው በዳርዮስ መንግሥት ዘመን ተጻፉ።

23የሌዊ ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች እስከ ኤልያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ዘመን ድረስ በታሪክ መጽሐፍ ተጻፉ።

24የሌዋውያኑም አለቆች፤ ሐሸብያ፥ ሰራብያ፥ የቀድምኤልም ልጅ ኢያሱ እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።

25መታንያ፥ በቅቡቅያ፥ አብድዮ፥ ሜሱላም፥ ጤልሞን፥ ዓቁብ በበሮች አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች ለመጠበቅ በረኞች ነበሩ።

26እነዚህ በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም በአለቃውም በነህምያ በጸሐፊውም በካህኑ በዕዝራ ዘመን ነበሩ።

27የኢየሩሳሌምንም ቅጥር በቀደሱ ጊዜ ቅዳሴውን በደስታና በምስጋና በመዝሙርም በጸናጽልም በበገናም በመሰንቆም ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑን በየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ።

29ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤ ሕዝቡንም በሮቹንም ቅጥሩንም አነጹ።

30የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፤ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፤ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጕድፍ መጣያው በር ሄደ።

31ከእነርሱም በኋላ ሆሻያ፥ የይሁዳም አለቆች እኵሌታ፥

32ዓዛርያስ፥ ዕዝራ፥

33ሜሱላም፥ ይሁዳ፥ ብንያም፥ ሸማያ፥ ኤርምያስ፥

34መለከትም ይዘው ከካህናቱ ልጆች አያሌዎች፥ የአሳፍም ልጅ የዘኩር ልጅ የሚካያ ልጅ የመታንያ ልጅ የሸማያ ልጅ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ፥

35ወንድሞቹም ሸማያ፥ ኤዝርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእግዚአብሔርን ሰው የዳዊትን የዜማውን ዕቃ ይዘው ሄዱ፤ ጸሐፊውም ዕዝራ በፊታቸው ነበረ።

36በምንጭም በር አቅንተው ሄዱ፤ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ።

37ሁለተኛውም የአመስጋኞቹ ተርታ ወደ ግራ ሄደ፤ እኔና የሕዝቡም እኵሌታ በስተኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ በእቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥ ከኤፍሬምም በር በላይ፥

38በአሮጌው በርና በዓሣ በር በሐናንኤልም ግንብ፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ።

39እንዲሁ ሁለቱ የአመስጋኞች ተርታዎች በእግዚአብሔር ቤት ቆሙ፤ ከእነርሱም ጋር እኔና የአለቆች እኵሌታ፥

40ካህናቱም ኤልያቄም፥ መዕሤያ፥ ሚንያሚን፥ ሚካያ፥ ኤልዮዔናይ፥

41ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥ መዕሤያ፥ ሸማያ፥ አልዓዛር፥ ኦዚ፥ ይሆሐናን፥ መልክያ፥ ኤላም፥ ኤጽር ቆምን። መዘምራኑም በታላቅ ድምፅ ዘመሩ፥ አለቃቸውም ይዝረሕያ ነበረ።

42እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ።

43ይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቍርባንና ለበኵራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ።

44እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዓት የመንጻታቸውንም ሥርዓት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ።

45አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ።

46እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፥ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።