መዝሙረ ዳዊት 134:1-3

Ethiopian Amharic Bible (AMH)

1እነሆ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ፥ በአምላካችን ቤት አደባባዬች የምትቆሙ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ።

2በሌሊት በቤተ መቅደስ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፥ እግዚአብሔርንም ባርኩ።

3ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ።