መዝሙረ ዳዊት 105:1-42

Ethiopian Amharic Bible (AMH)

1እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ።

2ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።

3በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።

4እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።

6ባሪያዎቹ የአብርሃም ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱን የአፉንም ፍርድ።

7እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው።

8ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥

9ለአብርሃም ያደረገውን፥ ለይስሐቅም የማለውን፤

10ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን እንዲሆን አጸና።

11እንዲህም አለ። ለአንተ የከነዓንን ምድር የርስታችሁን ገመድ እሰጣለሁ፤

12ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች፥ እጅግ ጥቂቶችና ስደተኞች ሲሆኑ ነው።

13ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥ ከመንግሥታትም ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ።

15በምድር ላይ ራብን ጠራ፥ የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ።

16በፊታቸው ሰውን ላከ፤ ዮሴፍ ለባርነት ተሸጠ።

17እግሮቹም በእግር ብረት ደከሙ፥ እርሱም በብረት ውስጥ ገባ።

18ቃሉ እስኪመጣለት ድረስ፥ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው።

19ንጉሥ ላከ ፈታውም፥ የአሕዛብም አለቃ አስፈታው።

20የቤቱ ጌታ፥ የጥሪቱ ሁሉ ገዢ አደረገው፥

21አለቆቹን እንደ ፈቃዱ ይገሥጽ ዘንድ፥ ሽማግሌዎቹንም ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ።

22እስራኤልም ወደ ግብጽ ገባ፥ ያዕቆብም በካም አገር ተቀመጠ።

23ሕዝቡንም እጅግ አበዛ፥ ከጠላቶቻቸውም ይልቅ አበረታቸው።

24ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ በባሪያዎቹም ላይ ይተነኰሉ ዘንድ ልባቸውን ለወጠ።

25ባሪያውን ሙሴን የመረጠውንም አሮንን ላከ።

26የተኣምራቱን ነገር በላያቸው ድንቁንም በካም አገር አደረገ።

27ጨለማን ላከ ጨለመባቸውም፤ በቃሉም ዐመፁ።

28ውኃቸውን ወደ ደም ለወጠ፥ ዓሦቻቸውንም ገደለ።

29ምድራቸው የንጉሦቻቸውም ቤቶች በጓጕንቸር ሞሉ።

30ተናገረ፥ የውሻ ዝንብ ትንኝም በዳርቻቸው መጡ።

31ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፥ እሳትም በምድራቸው ተቃጠለች።

32ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፥ የአገራቸውንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።

33ተናገረ፥ አንበጣም ስፍር ቍጥር የሌለውም ኩብኩባ መጣ፥

34የአገራቸውንም ለምለም ሁሉ በላ፥ የምድራቸውንም ፍሬ በላ።

35የአገራቸውንም በኵር ሁሉ፥ የጕልበታቸውን መጀመሪያ ሁሉ መታ።

36ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥ በወገናቸውም ውስጥ ደዌ አልነበረም።

37ፈርተዋቸው ነበርና ግብጽ በመውጣታቸው ደስ አላት።

38ደመናን ለመሸፈኛ ዘረጋባቸው፥ እሳትንም በሌሊት ያበራላቸው ዘንድ ዘረጋ።

39ለመኑ፥ ድርጭትንም አመጣላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው።

40ዓለቱን ሰነጠቀ፥ ውኃውም ፈሰሰ፤ ወንዞች በበረሃ ሄዱ፤

41ለባሪያው ለአብርሃም የነገረውን ቅዱስ ቃሉን አስቦአልና።

42ሕዝቡንም በደስታ የተመረጡትንም በእልልታ አወጣ።

43የአሕዛብንም አገሮች ሰጣቸው፥ የወገኖችንም ድካም ወረሱ፥

44ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ፥ ሥርዓቱንም ይፈልጉ ዘንድ። ሃሌ ሉያ