መዝሙረ ዳዊት 150:1-6

Ethiopian Amharic Bible (AMH)

እግዚአብሔርን በየነገሩ አመስግኑ

Amharic Bible. MIT-licensed data.

1ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በኃይሉ ጠፈር አመስግኑት።

2በችሎቱ አመስግኑት፤ በታላቅነቱ ብዛት አመስግኑት።

3በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት።

4በከበሮና በዘፈን አመስግኑት፤ በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት።

5ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት።

6እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።